
ግንቦት 15/2018ዓ.ም
የወልድያ ዩኒቨርሲቲን ላለፉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር አበበ ግርማ የሀላፊነት ቆይታ ጊዜያቸው መጠናቀቁን ተከትሎ አድስ ወደ ሀላፊነት ከመጡት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው ጋር በዛሬው ዕለት ከትምህርት ሚኒስተር የመጡ የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የስራ ርክክብ፣ የትውውቅና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሀ-ግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩም ከትምህርት ሚኒስተር የመጡ የስራ ሀላፊዎች ዶ/ር አብረሀም ገ/ዮሀንስና አቶ ደረጃ ተስፋየ ተቋሙ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሲያልፍ የነበሩትን ችግሮች ሁሉ ችለው ላለፉት ስድስት አመታት ተቋሙን ለመሩት ዶ/ር አበበ ግርማ ያከናወኗቸውን አንኳር ስራዎች በመጥቀስ እናመሰግናለን ብለዋል።
አያይዘውም አዲስ የተመደቡት ፕሬዝደንት ዶ/ ር አነጋግረኝ ጋሻው ከአሁን በፊት የነበራቸውን ልምድ በመጥቀስ እንደ ተቋም አመራር የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማስጨረስ፤ ከዞኑና ከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን መስራት እንዲሁም የተጀመሩ ስኬቶችን ማስቀጠል እንዳለባቸው በመጠቆም በሁለቱ ፕሬዝደንቶች መካከል የስራ ሰነድ ርክክብ እንዲካሄድ አድርገዋል።
የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶ/ር አበበ ግርማ በበኩላቸው ባሳለፍኳቸው ስድስት አመታት ውስጥ በርካታ ውጣውረዶችን ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አሳልፈናል ካሉ በኋላ ስለደገፋችሁኝም አመሰግናለሁ ብለዋል።
አዲስ የተመደቡት ፕሬዝደንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው አዲስ አመራር ሲባል ስራን ከአንድ የሚጀምር ሳይሆን የነበሩት አመራሮች የጀመሩትን ከዩኒቨርሲቲውና አካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ በመስራት ማስቀጠል መሆኑንጠቅሰው፤ የተጀመሩ ስኬቶችን በማስቀጠል፤ የጎደሉትን በመሙላትና ማደግ የሚገባቸውን በማሳደግ እንዲሁም ዘመኑየሚፈልገውን ስራ በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።
አክለውም የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንቶች በየትኛውም ዘርፍ ዩኒቨርሲቲውን እንድደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ተሳታፊዎችም ለሁለቱም ፕሬዝደንቶች ለወደፊት ስራቸው ስንቅ የሚሆኑ አስተያየቶችን በመስጠትና መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም የህጻናት ማቆያውን፣ በግንባታ ላይ ያለውን የአይሲቲ ዳታ ሴንተር፣የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ፣ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ኤፍኤም ሬድዮን ጨምሮ ሌሎች የተሰሩና እየተሰሩ ያሉስራዎችን ጎብኝተዋል።
ዘገባው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኘነት ነዉ
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel: https://t.me/Woldia_University
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.