
ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም
ግምገማው የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ የምርምር ካውንስል አባላቱና ተመራማሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
ጥናትና ምርምሮች ተሰርተዉ ሲጠናቀቁም ሆነ በሂደት ላይ እያሉ ለተሳታፊዎች ቀርቦ መገምገሙ ፋይዳው የጎላ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርየ በለጠ ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማሩና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በተጨማሪ ጥናትና ምርምር አንዱ ተልዕኮው በማድረግ ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች ጋር በማቀናጀት የተለያዩ የምርምር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በመሆኑም ዛሬ የሚገመገሙ ምርምሮችም የበጀት አጠቃቀማቸው፤ ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ውጤት ያስገኛል ወይ? በሚሉት ነጥቦች ላይ ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ በመገምገም መሻሻል ያለበት መሻሻል፣ መቋረጥ ያለበት ሊቋረጥ መበረታታት ያለበት ደግሞ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል።
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በጀት ተመድቦላቸው እየተሰሩ ያሉ 66 መምህራን የሚሳተፉባቸው በውስጣቸው 20 ንዑስ ጭብጦች ያሏቸው ስድስት ጭብጥ ተኮር የምርምር ስራዎች (ThematicResearches) ያሉበትን ደረጃ ለመፈተሽ ግምገማ መካሄዱን የዩኒቨርሲቲዉ የምርምር ህትመት ስነ-ምግባርና ስርዓት ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳልካቸው ፈቃዱ ገልጸዋል።
ግምገማው የሚካሄደው በጀቱ የተነሳበትን አላማ ማሳካቱን፣ በመጠናቀቅ ላይ ያሉት የምርምር ስራዎች በቀጣይ ምን መስራት አለባቸው? ዝግጅታቸው ምን ይመስላል? የሚሉትንና መሰል ጥያቄዎችን ለመመለስ ታስቦ መዘጋጀቱን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
አክለውም እንደየ ምርምሮቹ ባህሪ ታይቶ ለቀጣይ ወደ ማህበረሰብ የሚሸጋገሩበትን፣ በሳይንሳዊ መንገድ ለማህበረሰቡ የሚቀርቡበትን አቅጣጫ ለማስያዝ እንዲሁም መስተካከል ያለባቸውን ለማስተካከል ግምገማው በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በመጨረሻም ተመራማሪዎች የተሰጣቸውን አስተያየቶች በማካተት ምርምሮቹን ጽፈው አለማቀፍ ህትመቶች ላይ በማሳተም በሚቀጥለው ዓመት ወደ ችግር ፈች የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ተቀይረው ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ነው።
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel: https://t.me/Woldia_University
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.