ወልድያዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ሰብሳቢ ሆኖ ተመረጠ

መጋቢት11/2017 ዓ፣ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
የአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት በሚቆይ የአገልግሎት ዘመን የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አበበግርማን የፎረሙ ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል፡፡

የፎረሙሰብሳቢ የነበሩት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ የቆይታ ጊዜ ማጠናቀቃቸዉን ተከትሎ ፎረሙ ባደረገዉ አስቸኳ ስብሰባ በምትካቸዉ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የሆኑትን ዶ/ር አበበ ግርማን የፎረሙ ሰብሳቢ ሆነዉ እዲያገለግሉፎረሙ ወስኗል፡፡

“Togetherwe can make a difference!” ‹‹በጋራ ለዉጥ ማምጣት እንችላለን!›› በሚለዉ መፎክራቸዉ የሚታወቁት የአማራ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በስሩ በክልሉ ያሉ አስር ዩኒቨርሲቲዎችን ያቀፈ ሲሆን፤ ዋና አላማዉም ከመንግስት የተጣለበትን የከፍተኛ ት/ት ተቋም ሀላፊነት፡-በመማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ምርምሮችን በመስራት የቴክኖሎጅ ሽግግር በመፍጠር የማህበረሰቡን ችግር መፍታት ነዉ፡፡ በተጨማሪም ፎረሙ በክልላዊና ሀገራዊ አጀንዳዎችን ላይ ድምጽ በመሆን ክልላዊና ሀገራዊ ልማት እንዲያድግ ይሰራል፡፡ የአማራዩኒቨርሲዎች ፎረም ህጋዊ ምዝገባ ፈቃድ ካገኘበት የካቲት 2006 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ክልላዊና ሀገራዊ ስራዎች የሰራ ሲሆን ለአብነትም፤

– የኮቪድ 19 ምላሽ መስጠት የሚያስችል መፍትሄዎችን በመፈለግ፣
– በክልሉ ያለዉን ምርትና ምርታማነት ማሻሻል የሚያስችል የተሻሻለ የግብርናሜካናይዝድ አማራጮችን በማቅረብ፣
– በሰዉ ሀብት ግንባታ እና ስትራቴጅክ ፖሊሲ ቀረጻ ላይ በመሳተፍ፣
– ከክልሉ በሚገኙ ቢሮዎች፣ የልማት ድርጅቶች ግብረ-ሰናይ ተቋማት ጋር በመተባበር ምርምሮችን በመስራት
– የሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ የህብረተሰብ ክፍች ድጋፍ በማድረግና ት/ት ቤቶችን በመደገፍ… እና ሌሎች ስራዎችን በመስራት ላይ ያለ የከፍተኛ ት/ት ተቋማት ፎረም ነዉ፡፡
የወልድያ ዩኒቨርሲቲም የዚህ ትልቅ አላማ ባለቤት የሆነዉን የአማራ ዩኒቨርሲቲዎችፎረም የሰብሳቢነት ሚና ለተሰጣቸው ለዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝደንት ዶ/ር አበበ ግርማ እንኳን ደስ አለዎት እያልን፤ ዩኒቨርሲያችንም ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ፎረሙን የማስተባበር ሀላፊነት መወጣት ስላለበት የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ በሙሉ የፎረሙን አላማ በመገንዘብእና እዉን እንዲሆን የትብብር ሚናችንን ልንወጣ ይገባል፡፡

የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel : https://t.me/Woldia_University
YouTube : https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box : 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply