ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት)
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተቋሙን ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውይይትና የፊርማ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡
ተቋሙ ቁልፍ ተግባራትን ለመፈጸም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የአፈፃፀም ስምምነት ውል ከአሁን በፊት መፈራረሙን የተናገሩት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ፤ ዩኒቨርሲቲው በዋናነት መማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ጥናትና ምርምር መስራትና ማህበረሰብ አግልግሎት መስጠት እንዲሁም አስተዳደራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች ቀደም ሲል ተግባራዊ ሲደረጉ እንደቆዩ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ እያንዳንዱ ተግባራት ተደራጅቶና ተቀናጅቶ በዕቅድ ተመስርቶ በየጊዜው እየፈተሹ ቁልፍ ተግባራትን ከተቋሙ ዕቅድና የትኩረት መስኮች ጋር በማቀናጀት መፈጸም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ተግባራቶችን ለሁሉም መምህራንና ሰራተኞች ተደራሽ በማድረግ ያለንን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም ተረባርቦና ተቀናጅቶ በመስራት ተቋሙን የሚመጥንና የሚያንፀባርቅ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅ ተመላቷል፡፡
በዩኒቨርሲቲው በየዘርፉ የሚከናወኑ ቁልፍ ተግባራት ዕቅድ በስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈራ ተስፋዬ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ሁሉም የየድርሻውን በትኩረት ለመስራት ያስችል ዘንድ፤ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ ከዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርየ በለጠና ከአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር በላይ መንግስቴ ጋር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ስምምነት በመፈራረም የዕቅድ ሰነድ እርክክብ አድረገዋል፡፡በፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes!
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University
YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.