የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዘወልድ ባህል ማዕከል የሰሜን ወሎና ዋግኸምራ ዞን የማህበረሰብ እሴቶችን በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ለማስመዝገብ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክርአካሄደ።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዘወልድ ባህል ማዕከል የሰሜን ወሎና ዋግኸምራ ዞን የማህበረሰብ እሴቶችን በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ለማስመዝገብ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክርአካሄደ።

ሚያዚያ 9/2018ዓ.ም

በምክክር መድረኩበወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዘወልድ ባህል ማዕከል እና በቴክኖሎጂ ሽግግርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬቶች አዘጋጅነት የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከሰሜን ወሎና ዋግህምራ ዞን አስተዳደር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የመጡ ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው የግቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተካሂዷል።

ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አበበ ግርማ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ተልዕኮ በተቋቋሙበት አካባቢ ያሉትን የማኅበረሰብ እሴቶች በጥናት ተመርኩዘው እንዲሰነዱ፣ እንዲለዩና እንዲታወቁ ማድረግ ነው ብለዋል።

“ወሎ ከፍተኛ የባህል ክምችት ያለበት አካባቢ ነው” እነዚህን ባህሎች መደገፍና ከአካባቢው ተነስተው ለሀገር ብሎም ለዓለም እንዲበቁ ለማድረግ እንደ ዩኒቨርሲቲ በርካታ የምርምር ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል። የአካባቢውን ስነ-ምህዳርና መልክዐ-ምድራዊ ፀጋዎች መሰረት አድርገው የተሰሩ ስለሆነ እውቅና አግኝተው የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ ባለድርሻ አካላት ሰፊና ገንቢ አስተያየቶችን ልትሰጡ ይገባል ብለዋል።

የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርየ በለጠ በበኩላቸው አካባቢው ካለው የዳበረ ባህልና ወግ የተወሰኑትን ተመዝግበው እውቅና እንድያገኙ በዩኒቨርሲቲው ዘወልድ ባህል ማዕከል ዳይሬክቶሬት በሰሜን ወሎ እና በዋግኸምራ ዞኖች የሚገኙ የማኅበረሰብ እሴቶችን በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ለማስመዝገብ የልዬታና የዳሰሳ ጥናት ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የሰራነው ብዙ ባይሆንም የጀመርነው ብዙ ርቀት ያስኬደናል ብየ አምናለሁና የዛሬው ውይይትም አንድ ግብዓት ነው ብለዋል። ወርክሾፑን በሚመለከት የዘወልድ ባህል ማዕከል ዳይሬክተርና የፕሮግራሙ አዘጋጅ መ/ር ውቤ ታደገ ገለጻ አድርገዋል።

የወርክሾፑ ዓላማ የማህበረሰብ እሴቶችን በአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት ውስጥ ማስመዝገብ ከግለሰብ ፈጠራ በላይ ለሆነ የጋራ ቅርስ ጥበቃ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ የሰሜን ወሎና ዋግኸምራ ዞን የማህበረሰብ እሴቶችን በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከአላማዎቹ አኳያ እውቅና አግኝተው እንዲጠበቁ ለማድረግ ታስቦ የተካሄደ ወርክሾፕ መሆኑን መ/ር ውቤ አክለው ገልጸዋል።

የእውቅና አሰጣጥ ሂደትና የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተልዕኮዎች በተመለከተ ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በመጡት ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ታደሰ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበ ል።

‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel:  https://t.me/Woldia_University
YouTube:  https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply