ጥቅምት 16፣ 2017ዓ.ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
በትናትናዉ እለት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ባካሄደዉ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ከተወያየ በኋላ ዉሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
ከተወያየባቸዉ አጀንዳዎች መካከል፡ የዩኒቨርሲቲዉን የሴኔት ሌጅስሌሽን ረቂቅ መገምገም፣ አካዳሚክ ካሌንደር ማጽደቅ፣ የደረጃ እድገት፣ እጩ ተመራቂዎችን ምረቃ ማጽደቅ፣ የተለያዩ የመመሪያ ማሻሻያዎችን እና አዲስ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲጸድቅ ከቀረቡ በኋላ ዉሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡
በዚህም መሰረት፤
በእለቱም በሪጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት አቅራቢነት በተለያዩ መርሀ ግብሮች ትምህርታቸዉን በመጀመሪያ እና በሁለተና ዲግሪ ሲከታተሉ የነበሩ እጩ ተመራቂ ሁነዉ የቀረቡትን፤
. በመጀመሪያ ዲግሪ ወንድ፡ 6፣ ሴት፡ 7 ድምር፡13
. በፒዲቲ (PGDT) ወንድ፡1216፣ ሴት፡484 ድምር ፡1700
. በሁለተኛ ዲግሪ ወንድ፡ 103፣ ሴት፡ 24፣ ድምር፡ 127
ባጠቃላይ በሁሉም መርሀ ግብር ወንድ፡ 1325፣ ሴት፡ 513፣ በድምሩ፡ 1840 ተማሪዎች የሚጠበቅባቸዉን ስላሟሉ እንዲመረቁ ሴኔቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በተጨማሪም በትናንቱ የሴኔት ስብሰባ የሁለት መምህራንን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት የደረጃ እድገት ያጸደቀ ሲሆን፤
- Dr.Jenifer Lawrence from Management department Promoted to Associate Professor
- Dr.Prince Thomas from Information Technology Department promoted to associate Professor.
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በዛሬዉ እለት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማእረግ ያገኙ የስራ ባልደረቦችን እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡