
ወልድያ – የካቲት 02/2018ዓ.ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት) – በትምህርት ሚኒስቴር እና በአለም ባንክ ድጋፍ በጦርነት ለተጎዱ ዩኒቨርሲቲዎች ድጎማ የሚሆን የገመድ አልባ ኢንተርኔት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ትግበራን ተከትሎ የዝርጋታ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በድጋፍ ማእቀፉ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የገመድ አልባ የኢንተርኔት መሳሪያዎች በዩኒቨርሲቲው ገቢ ተደርገው ከሃምሌ 2017 እስከ ህዳር 2018 ዓ.ም ድረስ የፋይበር ዝርጋታና የኮንፊግሬሽን ሥራዎች ተከናውነዋል። ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የገመድ አልባ (Wireless) ኔትወርክ ፕሮጀክትን በተሳካ ሁኔታ ወደ አገልግሎት የገባ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ከታህሳስ 2018 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም ተገልጿል።
በፕሮጀክቱ አገልግሎት ላይ የዋሉት የኔትወርክ መሳሪያዎች መካከል: –
ዩኒቨርሲቲው ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ የአይሲቲ መሠረተ ልማቱን መልሶ ለመገንባት የገጠመውን ችግር ይህ ፕሮጀክት በከፊል መፍታቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በተለይ ለሴት ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ እና ለሌሎች ተማሪዎችና የተቋሙ ሰራተኞች ደግሞ በከፊል የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነትን እንዳሻሻለም የዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ መ/ር ጌታቸው ወርቁ ገልጸዋል።
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel: https://t.me/Woldia_University
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.