
ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት) –
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም አመላካቾችን /KPI’s/ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በተፈራረመው መሰረት፤ በዛሬው እለት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አበበ ግርማ (ዶ/ር) ከምክትሎቻቸው የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህ/አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ማርዬ በለጠ (ዶ/ር) እና የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዝዳንት በላይ መንግስቴ (ዶ/ር) እንዲሁም ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን አስማረ ጋር ተፈራርመዋል ፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት የሆኑት ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ ስራ አስፈፃሚዎች፣ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የቁልፍ ተግባራት አመላካች ገምጋሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል፡፡
በእለቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አበበ ግርማ (ዶ/ር) የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም አመላካቾችን /KPI’s/ በተመለከተ እንዲሁም ተቋሙ በተያዘው የበጀት ዓመት ትኩረት ሰጥቶ መሰራት ስለሚገባቸው ተግባራቶች ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከተሳታፊዎች በርካታ ሃሳብና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን፤ በተነሱት ሃሳቦች ላይ በተሰጠው የማጠቃለያ ምላሽ ከት/ት ሚኒስቴር ጋር የተፈራረምናቸው ሆኑ ዛሬ ከምክትል ፕሬዝደንቶች ጋር የተደረጉት ስምምነቶች የተቋሙን ተልእኮዎች ከማሳካት አንጻር ቁልፍ ተግባራቶች ተቆጥረው ሊመዘኑ በሚቻልባቸው አግባብ መሰራት እንዳለባቸው እና ለእያንዳንዱ ተግባራት መሳካት የሁሉም ሰራተኞች ድርሻና ርብርብ እንደሚጠይቅ ተመላክቷል።
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel: https://t.me/Woldia_University
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.