
ግንቦት 20/2017 ዓ.ም(የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
በዩኒቨርሲቲው በቴክ/ሽግ/ማህ/አገ ዳይሬክቶሬት አሰተባባሪነት በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን በልጽጎ ስራ ላይ የዋለው ሶፍትዌር በኢትዮጲያ አእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን (Ethiopian Intellectual Property Rights Authority) እውቅና አግኝቷል።
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት በፕሮጀክት ዘርፍ ከሚያከናውናቸው ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የወልድያ ከተማ የመሰረተ ልማት መምሪያ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን “ዲጂታል የመሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት” (Digital land information management system) ሶፍትዌር በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን በልጽጎ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።
ይህ ሶፍትዌር በኢትዮጲያ አእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን (Ethiopian Intellectual Property Rights Authority) ከአራቱ አእምሯዊ ንብረት መብቶች ዓይነቶች አንዱ የሆነው ቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች የሚባለው እውቅና ተሰጥቶታል ያሉት ሶፍትዌሩን ከሰሩት ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት መ/ር ደመቀ ጌታነህ ናቸው፡፡
መ/ር ደመቀ አክለውም ተቋሙ ሶፍትዌር አበልጽጎ በባለቤትነት ሲያስመዘግብ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ተቋሙ ይህን እውቅና ማግኘቱ እንደ ተቋም ትክክለኛ የፈጠራ ባለቤት እንደሆነ እውቅና ማግኘቱን ያረጋግጣል፡፡ ሌሎች ይህን ሶፍትዌር ለመጠቀም የተቋሙን ፍቃድ መጠየቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከተቋሙ ህጋዊ ፈቃድ ያላገኘ ማንኛዉም ድርጅት ወይም ግለሰብ ሶፍትዌሩን መቅዳት፣ ማሰራጨት ወይም ማሻሻልን ይከላከላል::
“ዲጂታል የመሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት” ለማሳለጥ የተሰራው ሶፍትዌር የተሰጠው እውቅና የአእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ መብት IPR (Intellectual property right) የባለቤትነት ማረጋገጫ እና አጠቃቀምን የመቆጣጠር ህጋዊ ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡
ይህ እውቅና የሶፍትዌር አበልጻጊዎች (developers) እና የፈጠራው ባለቤቶች(creators) ስራቸው የተጠበቀ መሆኑን አውቀው የተሻለ ለመፍጠር እንዲነሳሱ ያግዛል፡፡
የተሰጠው እዉቅና የፈጠራው ባለቤቶች ሥራቸውን በባለቤትነት መሸጥ ያስችላል፡፡ አንድ ሰው ወይም ተቋም ይህን ሶፍዌር ከገለበጠ ወይም አላግባብ ከተጠቀመበት ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንዲችል ያደርጋል የሚሉትንና መሰል ጠቀሜታዎች ለተቋሙ ያስገኛል፡፡
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከተሰጠው ተልእኮዎች አንዱ የማህበረሰቡን ችግር ፈች ጥናትና ምርምሮችን በመስራት፤ በጥናት በሚገኘው ግኝት በመነሳት ወደ ችግር ፈች የማህበረሰብ አ/ት ስራዎችና ፕሮጀክቶች መቀየር ይጠበቃል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አ/ት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተሰራው “ዲጂታል የመሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት” ሶፍትዌር አንዱ የዩኒቨርሲቲዎች ተልእኮ ማሳካት ማሳያ ነው፡፡
እውቅና ያገኘው ሶፍትዌር ለወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ አገልግሎት (ማዘጋጃ ቤት) አሰራሩን እንዲያዘምንበት፤ ከሙሉ ቁሳቁስና በቂ ስልጠና ጋር ዩኒቨርሲቲዉ ያበረከተ ሲሆን፤ ወደሌሎች ወረዳዎችና ከተሞች በህጋዊ መንገድ የሚስፋፋ ይሆናል፡፡
ሶፍትዌሩን ያበለጸጉት መምህራኖች ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተቀበሉትን የእውቅና ምስክር ወረቀት ለዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር፣ ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህ/ አገ/ት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ማርየ በለጠ በ7ኛ አመታዊ ምርምር ጉባኤ ማጠቃለያ መርሀ-ግብር አስረክበዋል፡፡
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel: https://t.me/Woldia_University
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.