የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የ2017 በጀት ዓመት የቁልፍ ተግባራት አመላካቾች (KPIs) ዕቅድ ክንውን ሪፖርትና በትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የሪፖርትና ዕቅድ ማስገቢያ ሲስተም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የ2017 በጀት ዓመት የቁልፍ ተግባራት አመላካቾች (KPIs) ዕቅድ ክንውን ሪፖርትና በትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የሪፖርትና ዕቅድ ማስገቢያ ሲስተም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

ሃምሌ 10/2017 ዓ.ም (የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት)

በየደረጃው ያሉ የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎች የ2017 በጀት ዓመት የቁልፍ ተግባራት አመላካቾች (KPIs) ዕቅድ ክንውን ሪፖርትና በትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የሪፖርትና ዕቅድ ማስገቢያ ሲስተም ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ስለበጀት ዓመቱ የቁልፍ ተግባራት አመላካቾች አፈጻጸም ሪፖርት በስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ ተስፋየ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር ስለተዘጋጀው የሪፖርትና ዕቅድ ማስገቢያ ሲስተም በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ በሆኑት መምህር ጌታቸው ወርቁ አማካኝነት ለተሳታፊዎች ቀርቧል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረቡትን የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ በርካታ ሃሳብ አስተያየቶችን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ያልሰራው በሰራው የሚወደስበትና የሰራው ባልሰራው የሚወቀስበት አግባብ የለም ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ KPI የተቋማትን ተልዕኮ ለማሳካት ያለመ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለእያንዳንዱ ነገር ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel:  https://t.me/Woldia_University
YouTube:  https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply