
ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም (የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት) – በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በኮሌጁ ስር ለሚገኙ መምህራንና ተመራማሪዎች በቴማቲክ የምርምር ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በትናንትናው ዕለት ተሰጥቷል።
የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በተበታተነና በተናጠል ሲሰራ የነበረውን የምርምር አሰራርን በማስቀረት ተመሳሳይ ጭብጥ ያላቸውን የምርምር ፕሮጀክቶችን ወደአንድ አምጥቶ ለመተግበር ያለመ መሆኑን የተናገሩት የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ዶ/ር አብዱራህማን አህመድ ናቸው፡፡
አስተባባሪው አክለውም ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸውን የምርምር ፕሮጀክቶችን ወደአንድ አምጥቶ መተግበሩ ወጭንም ሆነ ጊዜን እንዲሁም ችግሮችን ለይቶ ከመፍታት አንጻር ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይ ተሳታፊ መምህራንና ተመራማሪዎቹ የቴማቲክ ምርምር የአጻጻፍ ዘዴን በመከተልና በመተግበር ችግር ፈች፤ የተሻሉና ውጤታማ ምርምሮችን ይጽፋሉ ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል።
አጠቃላይ ስለቴማቲክ የምርምር ፕሮጀክት ምንነት፤ የአተገባበር ጽንስ ሃሳብና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መነሻ ጽሁፍ በዩኒቨርሲቲዉ የምርምር ህትመት ስነ-ምግባርና ስርዓት ዳይሬክተር በዶ/ር እንዳልካቸው ፈቃዱ አማካኝነት የተብራራ ሲሆን፤ የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረበውን የመነሻ ጽሁፍ መሰረት በማድረግ ሃሳብና አስተያየቶችን አቅርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel: https://t.me/Woldia_University
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.