የኢትዩጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ የእግርኳስ ፕሮጀክት የኳስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዩጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ የእግርኳስ ፕሮጀክት የኳስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት)

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ማህበረሰብ በተለይም ታዳጊ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ የሚታሰብ ከ2016ዓ ም ጀምሮ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት የታቀፉ በእግር ኳስና መረብ ኳስ ወንዶች እንዲሁም በአትሌቲክስ ሁለቱንም ጾታ ያካተተ የታዳጊ ህጻናት ስፖርት ፕሮጀክት አቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በዓመቱ መጨረሻ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የምዘና ውድድር ቅድመ ዝግጅት የሚሆን የኢትዩጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ፕሮጀክት የኳስ ድጋፍ ማድረግ መቻሉ በዩኒቨርሲቲው የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና የእግር ኳስ ፕሮጀክት አሰልጣኝ የሆኑት መምህር ዑመር ካሳ ተናግረዋል፡፡

ፌደሬሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የፓይለት ፕሮጅክት ከፍቶ እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት አሰልጣኙ ከተቋሙ ጋር ባደረግነው መልካም ግንኙነት ዩኒቨርሲቲው እየሰራ ያለውን በፌደሬሽኑ በኩል እውቅና በማግኘቱ ድጋፉን ሊያደርግ ችሏል ብለዋል።

ፌደሬሽኑ በቀጣይ ልክ እንደሌሎቹ ፓይለት ፕሮጀክቶች ጋር እኩል ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን በመጠቆም ለተደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ውጤታማ ለማድረግ በፌደሬሽኑ ከተደረገው የኳስ ድጋፍ በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በኩል የተገዙ የስፖርት ጫማና ልብስ (ሙሉ የስፖርት ትጥቅ) ለሁሉም የፕሮጀክቱ ሰልጣኞች ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዕለቱም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርየ በለጠና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ ቢሆንን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች በቦታው ተገኝተው የፕሮጀክቱን ሰልጣኝ ታዳጊ ወጣቶቹን አበረታተዋል፡፡

ቀደም ሲል በወልድያ መምህራን ኮሌጅ ስፖርት ሜዳ ሲሰጥ የነበረው የታዳጊ ህጻናት ስፖርት ፕሮጀክት ስልጠና በዚህ ዓመት የትራንስፖርት አገልግሎት ተመቻችቶ ወደዩኒቨርሲቲው በማምጣት በዘርፉ የረጀም ጊዜ ልምድ ባላቸው መምህራን ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ የሜዳ ላይና በመሳሪያ የታገዘ ስፖርታዊ ልምምድ እንዲሁም ከስልጠና መልስ ያወጡትን ላብ በመተካት ዉጤታማ አካላዊ ለዉጥ ያመጡ ዘንድ በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ የምገባ አገልግሎት እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

አካባቢው ሰፊ የስፖርት ሃብት ያለው በመሆኑ ፕሮጀክቱ በቀጣይ በስፖርቱ ዘርፍ ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡

‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel:  https://t.me/Woldia_University
YouTube:  https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply