የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አቀፍ ሞዴል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አቀፍ ሞዴል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡

ሚያዝያ 18/2017ዓ.ም. (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኑነት) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አቀፍ ሞዴል ት/ት ቤት ለመገንባት የወልድያ ከተማ ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬን ጨምሮ ሌሎች የጽ/ቤት ሀላፊዎችና የማህበረሰቡ ተወካዮች በተገኙበት ሚያዝያ 18/2017ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሀ-ግብር ተካሄዷል፡፡

በመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሀ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር፣ የቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አ/ት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርየ በለጠ ስፋቱ 21003 ካሬ ሜትር የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ከወልድያ ከተማ ክቡር ከንቲቫ አቶ ዱባለ አብራሬ እጅ ተረክበዋል፡፡
በመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ ዶ/ር ማርየ በለጠ ተቋሙ የት/ት ተቋም በመሆኑ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጥንለት የማህበረሰብ አቀፍ ሞዴል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞች ልጆችን ጨምሮ በአካባቢዉ የሚገኙ የማህበረሰብ ልጆችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነዉ ብለዋል፡፡
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠዉ ተልዕኮ አንጻር የአካባቢዉን ማህበረሰብ በት/ት፣ በጤና፣ በታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክት፣ በውሀ አቅርቦትና ከተማውን ለማልማት በርካታ የዲዛይን ስራዎችን በመስራት የከተማ አስተዳደሩንና ማህበረሰቡን እያገዘ መሆኑን አውስተዉ በከተማው ማህበረሰብ ስም ዩኒቨርሲቲዉን አመስግነዋል፡፡

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሀላፊነትን ከመወጣት አንጻር እየሰራቸዉ ከሚገኙ በርካታ ስራዎች ትምህርት አንዱ በመሆኑ፣ በወልድያ ከተማ በጣይቱ ክፍለ ከተማ አድማስ ባሻገር ቀበሌ ከመምህራን አፓርታማ ወረድ ብሎ በሚገኘዉ አካባቢ በተቀበለዉ 21003 ካሬ ሜትር ስፋ ያለዉ ቦታ ላይ ት/ት ቤቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኖች ልጆችን እና በዙሪያዉ ያሉ ማህበረሰቡ ልጆች እንዲማሩበት ከማድረጉም በተጨማሪ፣ ት/ት ቤቱ ለትምህርትና ስነ- ባህሪ ኮሌጅ ሞዴል የምርምር ማእከል እንደሚሆን ይታመናል፡፡

———————————————————————————————-

‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››

የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https:/wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel : https://t.me/Woldia_University
YouTube : https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply