ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣ ልዑክ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ጋር በቁልፍ ተግባራት አመላካች (KPI) ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣ ልዑክ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ጋር በቁልፍ ተግባራት አመላካች (KPI) ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

በተቋሙም ተዘዋውረው ምልከታዎችን አድርገዋል።

ሚያዝያ 04/2017ዓ.ም (የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

ከት/ት ሚኒስቴር የመጡ ልዑክ ከትናንትና ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ሰራተኞች ጋር በKPI ዙሪያ ውይይቶችንና ምልከታዎችን አድርጓል። ልዑኩ በትናንትናው ዕለት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ከተውጣጡ መምህራን፣ የአሰተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች ጋር በተናጠል ውይይቶችን ያካሄዱ ሲሆን፤ ለሁሉም በየደረጃው ላሉ የስራ ኃላፊዎችም ስለትምህርት ሚኒስቴር ሪፎርምና የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

ልዑኩ በዛሬው ዕለትም በዩኒቨርሲቲው የተሰሩትንና በመሰራት ላይ ያሉ መሰረተ ልማቶችን የጎበኙ ሲሆን በተለይም የኪችን ኮምፕሌክስና በመገንባት ላይ ያለውን የሪጅስትራር ህንጻዎች፣ በዕድሳት ላይ ያሉትን የመረብ፤የእጅና ቅርጫት ኳስ ሜዳዎችን፣ የታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክትን እና የተማሪዎች ምግብ ማብሰያን ጎብኝተዋል። በተጨማሪም በጉብኝታቸው ከሶስት ዓመት በፊት በነበረው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ሙሉ ለሙሉ ውድመት ደርሶባቸው ወደአገልግሎት የተመለሱ፣ ገና ያልተመለሱ ላብራቶሪዎችንና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን ተንቀሳቅሰው ተመልክተዋል። ባደረጓቸው የተለያዩ ውይይቶችና ተንቀሳቅሰው ባዩት የስራ እንቅስቃሴ መሰረት የለዩአቸውን ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተደራሽነትን ለማስፋት በርካታ የለውጥ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት በትምህርት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ፋሲሊቲ ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰይድ መሃመድ በዋናነት ምልከታው በዩኒቨርሲቲዎችና በትምህርት ሚኒስቴር ውጤት አመላካቾችን ለይተው በወሰዱት ስምምነት መሰረት ምን ያህል እየሄዱ እንደሚገኙ ለማየትና ለመገምገም ነው ብለዋል። በምልከታው በተቋሙ የተሻለ የስራ እንቅስቃሴ እንዳለ ማየት መቻላቸውን የተናገሩት ኃላፊው አንዳንድ ክፍተቶች እንዳሉ ሁነው ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ የተግባር አፈጻጸሞችንም መመልከታቸውን ገልጸዋል።

የተደረገው ምልከታና የተሰጡ  አስተያየቶች ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ የቁልፍ ተግባራትን ትኩረት ሰጥቶ ለመፈጸም ያስችላል ያሉት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ ለተደረገው እይታም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ተቋሙ ቀደም ሲል በነበረው ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ውድመት የደረሰበት በመሆኑ በቀጣይ ይበልጥ ስራን ሊያሰራና ሊያሳልጥ የሚችል፤ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ በጀትን ጨምሮ የግብዓትና ሌሎች ድጋፎች ቢደረግና በትኩረት ቢታይ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። በቀጣይ የተግባር አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ለመቀጠልና ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማንኛውንም የሚጠበቅበትን ሚና ለመወጣት ይሰራል ብለዋል አቶ ሰይድ መሀመድ።

___________________________________________________________________________

‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https:/wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel : https://t.me/Woldia_University
YouTube : https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

ማስታወሻ

ወቅታዊ እና አዳዲስ መረጃዎች ከፌስቡክ እና ቴሌግራም ገፆቻችን በተጨማሪ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገፅ ላይ ይከታተሉ።

Recent News

Unlock the Potential of Super Ace Auto-Play Feature
April 24, 2025By
Meet Your Host: A Guide to Personalized Service and VIP Access
April 24, 2025By
Memorandum of Understanding (MoU) Signed Between Woldia University and Vinayaka Mission’s Research Foundation (Deemed-to-be University), India
April 14, 2025By

Leave a Reply