ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር የቢሮ ዲዛይን ሰርቶ አስረከበ

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር የቢሮ ዲዛይን ሰርቶ አስረከበ

መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት)
በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ማእቀፍ በጀት በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን የተሰራ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ቢሮ ባለ 4 ወለል (G+4) የህንጻ ዲዛይን ስራ ተጠናቆ እርክክብ ተካሄደ። በርክክቡ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርየ በለጠ ተቋሙ ከሚሰራቸው በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች መካከል አንዱ ያለውን ዕውቀትና ሙያን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ተጠቅሞ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዲዛይን ስራው ላይ ለተሳተፉ መምህራንና ተመራማሪዎች ምስጋና ያቀረቡት ም/ፕሬዝዳንቱ ጊዜ፣ ጉልበትና በጀት ፈሰስ ተደርጎበት ወረቀት ላይ ያለው የዲዛይን ስራ ወደ መሬት ወርዶ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ሲሆን ማየት ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት መምህርት ሰላማዊት አባይ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ከተለያዩ የሙያ መስኮች የተዉጣጡ 18 መምህራንን በማሳተፍ የተሰራ ሲሆን፤ በስራዉ ወቅት ቦታዉን ከማየት ጀምሮ አስፈላጊዉን መረጃ በመሰብሰብ፤ የዲዛይን ስራዉ መነሻ ሀሳብ ታሪካዊ ገላጭነትን እና ለዘመናዊ የቢሮ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የቅዱስ ላሊበላ (የቤተ-ጊዮርጊስ) ቅርጽ በሚገልጽ መልኩ መሰራቱ ተገጧል፡፡ የተሰራውን የህንጻ ዲዛይን በዶ/ር ማርየ በለጠ በኩል የሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ አለምፀሃይ ከበደ የተረከቡ ሲሆን፤ በርክክቡ ወቅት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሚያምረው ጌጤ ለታዳሚዎች ቀጥታ በስልክ በሰጡት አስተያየት ዩኒቨርሲቲው ለብሄረሰብ አስተዳደሩ ያለውን አጋርነት አጉልቶ የሚያሳይና የሚያጠናክር ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል በማለት ያላቸውን ምስጋናም አቅርበዋል፡፡

‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https:/wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel : https://t.me/Woldia_University
YouTube : https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply