የተቋሙን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ህዳር 02/2017 ዓ.ም. (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
የተቋሙን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ እየሰራ የሚገኘው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሃብት ልማትና ገቢ ማመንጫ ጽ/ቤት የውስጥ ገቢን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከፍራፍሬና አትክልት፣ ከማር ምርት፣ ከሳር ሽያጭ፤ ለተለያዩ አገልግሎት ከሚሰጡ ቤቶች እንዲሁም ከእርሻ መሬት ኪራይና ከሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ሽያጭና ኪራይ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በርቀትና ተከታታይ ትምህርትና ሌሎች ዘርፎች የሚገኘውን ገቢ ሳይጨምር 3,520,995 (ሶስት ሚሊየን አምስት መቶ ሃያ ሽህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አምስት ብር) ገቢ መገኘቱን የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሃብት ልማትና ገቢ ማመንጫ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዋጋዬ ሞላ ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው የውስጥ ገቢ በተሻለ መልኩ በያዝነው 2017 በጀት ዓመት ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ስራ አስፈጻሚዋ በበጀት ዓመቱ 4,579,339 ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ እንዳለና መምህራን ለሰርቶ ማሳያነት በሰሯቸው ፕሮጀክቶች የተገኘውን ገቢ ጨምሮ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1,227,266 ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።

የተቋሙን የውስጥ ገቢ ሊያሳድጉ የሚችሉ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ ማንኛውም የሃብት ምንጭ በሚሆኑ ዙሪያ ላይ አተኩሮ ለመስራትና ገቢውን ለማሳደግ ከሚመለከታቸው ፋኩልቲዎች ጋር በመሆን የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ኮሚቴ ተዋቅሮ በጥናት ላይ እንደሚገኝ ወ/ሮ ዋጋዬ አክለው ገልጸዋል።
በቀጣይም ያሉ የሃብት ምንጮችን በማጠናከርና ሌሎችንም በመጨመር ዕቅዱን ለማሳካትና ገቢውን ለማሳደግ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በግቢው ውስጥ ለግቢው ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ካፊዎች የገቡትን ውል አክብረው እንዲሰሩ ያሳሰቡት ወ/ሮ ዋጋዬ አንዳንድ ካፊዎች የተሰጣቸውን የዋጋ ዝርዝርና የገቡትን ውል ወደጎን በመተው ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ካፊዎች ላይ ሂደቱን ጠብቆ አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝና ወደፊትም ማስተካከያ የማያደርጉ ካፌዎች ካሉ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።


አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes!
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://www.wldu.edu.et/
Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University
YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply