ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች “Public Entrepreneurship and Innovation Ecosystem Building ( PEIEB)” ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ህዳር 9/2017 ዓ.ም(ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኘነት)
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከኢንተርፕሬነርሺፕ ልማት ኢንስትቲዩት – Entrepreneurship Development Institute(EDI) ከክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለፕሬዝዳንቶች፣ዲኖች፣ዳይሬክተሮች እና ልዩ ረዳቶች ስልጠናውን በመሰጠት ላይ ይገኛል።
ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዝደንና የስልጠናው አስተባባሪ ዶ/ር በላይ መንግስቴ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ይህ ስልጠና የስራ አመራሮች ስለ ስራ ፈጠራና የስራ ፈጠራ ዘርፉን የሚደግፍና የሚመራ አመራርና ተቋም ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
ዶ/ር በላይ መንግስቴ አክለውም ስልጠናው እንደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ እስከ አሁን የመጣንበትን አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግና በስራ ላይ እንዴት ውጤታማ እንሆናለን? ምንስ መስራት ይጠበቅብናል? የሚሉትንና መሰል ጥያቄዎች ለመመለስ ወሳኝ በመሆኑ በትኩረት ልትከታተሉ ይገባል ብለዋል።
ስልጠናው በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ከኢንተርፕሬነርሺፕ ልማት ኢንስትቲዩት ተቋም በመጡ አሰልጣኞች በዶ/ር ክንድየ ኢሳ (መምህር፣ አሰልጣኝ፣ እና የቢዝነስ አማካሪ) እንዲሁም በአቶ አባተ ሀይሉ (መምህር፣ አሰልጣኝ፣ እና የቢዝነስ አማካሪ) ሲሆኑ፤ ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት እየተሰጠ ይገኛል።
አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes!
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://www.wldu.edu.et/
Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
tyrdzgh