ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝም ሚኒስቴር የተዘጋጀውን 5ኛውን የቱሪዝም ዘርፍ ጥናትና ምርምር ጉባኤ አንዱ ባለድርሻ በመሆን አከበረ።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝም ሚኒስቴር የተዘጋጀውን 5ኛውን የቱሪዝም ዘርፍ ጥናትና ምርምር ጉባኤ አንዱ ባለድርሻ በመሆን አከበረ።

መስከረም 15፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ (የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት)

ቱሪዝም ሚኒስቴር ‘ቱሪዝም ለዘላቂ ለውጥ’ በሚል መሪ ቃል 5ኛውን የቱሪዝም ዘርፍ ጥናትና ምርምር ጉባኤ መስከረም 15፣ 2018 በአዲስ አበባ አካሂዷል።

በጉባኤው የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ፣ የቱሪዝም መዳረሻና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ስለሽ ግርማ፣ የቱሪዝም ፕሮሞሽን እና ግብይት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር እንደገና አበበ እና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የተከበሩ አበባው አያሌውን ጨምሮ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና ተመራማሪ ምሁራን ተገኝተዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትሯ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ቱሪዝም በሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ሚና ካላቸው ዘርፎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህ የዓለም የቱሪዝም ቀን ሳምንት ይህንን የቱሪዝም ዘርፍ ጥናት ጉባኤ ስናከብር ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው የቱሪዝም ጥናቶች ቀርበው ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንዲደረግባቸው እና በሚሰጡ ምክረ ሀሳቦች ላይ ሚኒስትሩ በዕውቀትና መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲሰጥ ያስችላል ብለዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም ይህ ጉባኤ ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርገው ከሚሰሩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ መስራትን ለማጠናከር አይነተኛ ጅምር ይሆናል ብለዋል።

በዚህ አመታዊ የቱሪዝም ጉባኤ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና መዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ቱሪዝም ጋር በተያያዘ ያሉበትን ሁኔታ እና ቀጣይ ተግባራቶቻቸው ላይ ትኩረት ያደረገ ገለጻ አድርገዋል ።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲን በመወከል በምርምር፣ አለማቀፋዊነትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ስር የምርምር አለማቀፋዊነት አስተባባሪ የሆኑት በዶ/ር ጌትነት ዘለቀ አማካኝነት ቱሪዝም አንዱ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነና አካባቢው ለቱሪዝም ያለውን ፀጋዎች ለታዳሚዎች አጋርተዋል።

ቱሪዝም የተቋሙ አንዱ የልህቀት ማእከል እንዲሆንና ይህን እውን ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ምን እየሰራ እንደሆ እና ለወደፊት ምን እንደሚሰራ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ቱሪዝም ዘርፍን አንዱ አድርጎ ሲሰራ በተለይ በ Cultural heritage tourism, Eco-tourism and Peace tourism ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራና ቱሪዝም የሁሉንም ሴክተር ትብብር የሚሻ በመሆኑ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ለመስሳት ለሁሉም ጥሪ ተላልፏል።

በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ የምስጋና እውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
Web site: https://wldu.edu.et/
Facebook : https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel:  https://t.me/Woldia_University
YouTube:  https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw
P.O.Box = 400
Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Leave a Reply